አዉሮጳን ያስጨነቀዉ የጸጥታ ጉዳይ
ሐሙስ፣ መጋቢት 15 2008ማስታወቂያ
ባለፈዉ ሳምንት በፓሪስ ጥቃት ተፈላጊዉን ግለሰብ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ዒላማቸዉን እንዲለዉጡ እንዳደረገቸዉም ያትታሉ። የቤልጅየም ባለስልጣናት በቂ የስለላ ክትትል ባለማድረግ እና በጀትም ባለመመደብ ትችት ገጥሟቸዋል። ቱርክ ከጥቃት አድራሾቹ አንዱን አስራ እንደነበር እና ወደ ቤልጅየም ሲመለስም ለባለስልጣናቱ ማሳወቋን ይፋ ማድረጓም ሌላ ስጋትና ትችትን ነዉ ያስከተለባቸዉ። እራሱን እስላማዊ መንግሥት ከሚለዉ ፅንፈኛ እስላማዊ ቡድን ጋር ግንኙነት ያላቸዉ በርካቶችም ኢራቅና ሶርያ እየደረሱ ወደአዉሮጳ መመለሳቸዉም ሌላዉ የስጋት ምክንያት ሆኗል። የአዉሮጳ ኅብረት የሀገር ዉስጥ ሚኒስትሮች ጸጥታን በተመለከተ ዛሬ ስብሰባ ያካሂዳሉ። ስለብራስልስ ዉሎና ስለስብሰባዉ ገበያዉ ንጉሤን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሞ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ገበያዉ ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ