አወዛጋቢው የድንበር መከፈት ጉዳይ በጀርመን
ሐሙስ፣ መጋቢት 29 2008ማስታወቂያ
የጀርመን የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ቶማስ ደ ሚዜር ጀርመንን ከኦስትሪያ ጋር የሚያዋስናት ድንበር በቅርቡ ሊከፈት እንደሚችል መናገራቸው ያስነሳው ውዝግብ እልባት አላገኘም ። ስደተኞች በብዛት ወደ ጀርመን የሚገቡበት የደቡባዊ ጀርመንዋ የባቫርያ ፌደራዊ ክፍለ ሃገር አስተዳዳሪና የጀርመን ተጣማሪ መንግሥት አካል የሆነው የክርስቲያን ሶሻል ህብረት ፓርቲ ድንበሩ ይከፈታል መባሉን ተቃውሟል ። የፓርቲው መሪ የባየርን ጠቅላይ ሚኒስትር በጉዳዩ ላይ ትናንት በርሊን ውስጥ ከጀርመን መራሄ መንግሥትና ምክትል መራሄ መንግሥት ጋር ተነጋግረዋል ። ስለ ውዝግቡና ስለ ንግግሩ የበርሊኑን ወኪላችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ