አወዛጋቢው የዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት ብይን
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 20 2002ማስታወቂያ
« ማንም ዕውቅ ዓለም ዓቀፍ ተሰሚነት ያለው ኃይል በዚህ በጣም ጠባብ አሰተሳሰብ በተሰጠ የፍርድ ቤት ብይንና እና ቴክኒካዊ ውሳኔ በኮሶቮ ላይ ያለውን አቋም ይለውጣል ብዮ አልጠብቅም ።ሰርቢያን በተመለከተ እርግጥ ነው የህገ መንግስታችንን አቋም በምንም ዓይነት አንለውጥም »
የሰርቢያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቩክ የርሚክ
ኔዘርላንድስ ዴንሀግ የሚገኘው ዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት የኮሶቮ ነፃነት ዕወጃ ዓለም ዓቀፍ ህግን የጣሰ አይደለም ሲል ባለፈው ሳምንት የሰጠው ይህ ብይን ኮሶቮን ተጨማሪ ዕውቅና ለማግኘት ሲያተጋ ፣ ሰርቢያን ደግሞ በኮሶቮ ጉዳይ ላይ አዲስ ድርድር እንዲካሄድ ጥያቄ ለማቅረብ አነሳስቷል ። የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ