አከራካሬው የወንዶች ልጆች ግርዛት በጀርመን
ማክሰኞ፣ ሰኔ 26 2004የኮሎኝ የጀርመን ፍርድ ቤት ባለፈው ሳምንት ወንዶች ልጆችን መግረዝ በአካል ላይ ጉዳት ማድረስ ነው ሲል ያሳለፈው ውሳኔ እያወዛገበ ነው ። ይህ ውሳኔ ያስነሳው ክርክር የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው በዓለም የጤና ድርጅት ግምት ከዓለማችን ወንዶች 1/3 ተኛው ተገርዘዋል ። ከነዚህም አብዛኛዎቹ ሙስሊሞች አይሁዶች ና ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ናቸው ። በአንዳንድ ባህሎችም ከጤናና ከንፅህና አጠባበቅ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ወንዶች ይገረዛሉ ።የወንዶች ልጆች ግርዛት በአንዳንድ ሃይማኖቶች የማይቀር ልምድ ሲሆን ግርዛት በባህል አስገዳጅነት የሚከናወንባቸው ሁኔታዎች አሉ ። ወንዶች የሚገረዙበት እድሜ እንደ ሃይማኖቱ ባህሉና ይለያያል ። አይሁዶች ወንድ ልጅ በተወለደ በስምንተኛው ቀን ይገርዙሉ ። በሙስሊሞችም ሆነ በአንዳንድ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ዘንድ ወንዶች ልጆች በህፃንነታቸው ወይም ከፍ ሲሉ መገረዛቸው ሲወርድ ሲዋረድ የመጣና አሁንም በየአካባቢው የሚከናውወን ልምድ ነው ። በአንዳንድ ባህሎች ደግሞ ግርዘት ቤተሰብ ተሰባስቦ በድግስና በፈንጠዝያ የሚያከብረው ስርዓት ነው ። ጀርመንን ጨምሮ በብዙ የዓለም ክፍል የሚከናወነውን ይህን የተለመደውን
የወንዶች ግርዛት የምዕራብ ጀርመንዋ የኮሎኝ ከተማ ፍርድ ቤት ህገ ውጥ ና በአካል ላይ ጉዳት ማድረስ ሲል ተቃወሞታል ።ድርጊቱ በወላጆች ስምምነት ቢፈፀምም እንኳን የጀርመንን ህግ ይፃረራል ሲል የወንዶች ልጆችን ግርዘት ተቃውሞ ውሳኔ አሳልፏል ። ውሳኔው ብዙዎችን ግራ አጋብተል ። ከሙንስተር ዩኒቨርስቲ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት ዶክተር ሞግሃደም ፋታህ በወላጆች ፈቃድ የሚካሄደው ግርዛት ቀላልና የጤና ጠንቆች የማስከተሉ ሁኔታም እጅግ ዝቅተኛ ነው ። የሚታወቁ የጤና ጥቅሞችም እናዳሉት እየታወቀ የኮሎኙ ፍርድ ቤቱ በአንድ አጋጣሚ መነሻነት ይህን መሰል ውሳኔ ማሳለፉ ብዙዎች ያደናግራል ይላሉ ።
«እንደሚመስለኝ በኮሎኝ ፍርድ ቤት የተላለፈውን ብይን ጉዳዩ በሚመለከታቸው ወላጆችን ግርዘትን በሚፈፅሙና ለመፈፀም ምንጊዜም ዝግጁ በሆኑ ሐኪሞችና ክሊኒኮች ዘንድ በጣሙን ግራ የሚያጋባ ሁኔታ ነው የሚፈጥረው ። »
የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ጀርመን የሚገኙ የአይሁድና የሙስሊም ማህበረሰቦችን አስቆጥቷል ። ጀርመን የሚኖሩ ሙስሊሞችን ከሚያስተባብረው ምክር ቤት አሊ ኪዚልካያ ውሳኔውን የሰሙት ከታላቅ ሃዘን ጋር መሆኑን ነው የተናገሩት ። በርሳቸው አገላለፅ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በሃይማኖት ጉዳዮች በሰፊው ጣልቃ የሚገባ ነው ። በሺህ ዓመታት ለሚቀጠር ዘመን ሲፈፀም የቆየን ልማድ የኮለኙ ፍርድ ቤት ህገ ወጥ ሲል መበየኑ ለእምነቱ ተከታዮች አስገራሚ እንደሆነ ነው ኪዚልካያ የተናገሩት ። በራሳቸው አገላለፅ ይበልጡን የሚያስደንቀው ይህ ዓይነቱ ውሳኔ የተላለለፈው በጀርመን ብቻ መሆኑ ነው ። ካዚካልያ በመላው ዓለም በአሜሪካም የወንዶች ግርዘት ሳይከለከል በጀርመን ህገ ውጥ መባሉ ሊገባቸው ያልቻለ ጉዳይ ነው ። ከእስልምናም ሆነ ከሌሎች ህይማኖቶች አስቀድሞ የነበረን የሰው ልጆች ልምድ ህገ ወጥ መባሉን ሊረዱት አልቻሉም
ሙዚቃ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
እስከዛሬ በጀርመን በየሆስፒታሉና በየክሊኒኩ ህጋዊ ሆኖ ሲፈፀም የቆየው ግርዛት እንዲህ ትልቅ ጉዳይ ሆኖ ፍርድ ቤት ሊደርስ የበቃው የ4 ዓመት ሙስሊም ወንድ ልጅ ከተገረዘ በኋላ ለውስብስብ የጤና ችግሮች በማደረጉ ነው ። ልጁ ከተገረዘ ከጥቂት ቀናት በኋላ ከባድ የደም መፍሰስ ስላጋጠመው ተመልሶ ወደ ሐኪም ቤት ይገባል ። ከዚህ በኋላም አቃቤያነ ህግ ልጁን የገረዘውን ሐኪም በልጁ አካል ላይ ከባድ ጉዳት በማድረስ ከሰውታል ። ፍርድ ቤቱ ድርጊቱ ህገ ወጥ መሆኑን ስለማያውቅ በርሱ ላይ መፍረዱ አግባብ አይደለም ሲል ሐኪሙን በነፃ አሰናብቶ ስለራሳቸው መወሰን የማይችሉ ህፃናትን በሃይማኖት ሰበብ መግረዝ በአካላቸው ላይ ጉዳት ማድረሰ ነው ሲል ወስኗል ። ፍርድ ቤቱ በዚሁ ውሳኔው በጉዳዩ ላይ ከወላጆች መሰረታዊ መብቶች ይልቅ የህፃኑ አካል እንዳለ ተጠብቆ የመቆየቱ መብት ሚዛን ይደፋልም ሲል ነው ያስታወቀው ። በዚህ ውሳኔ ክፉኛ ያዘኑት የአይሁድ ማህበረሰብ ተጠሪ አሮና ራን ቬርኒኮቭስኪ በይሁዲ እምነት ግርዘት ከጥንታዊዎቹ ትዕዛዛት አንዱ መሆኑንና ከእግዚአብሔር ጋራ የሚያስተሳስራቸው ና የእምነታቸውም መሰረት መሆኑን ነው ያስረዱት ። ግርዘት ከአይሁዶች ሊለይ የማይችል መሆኑን ያስረዱት ቬርኒኮቭስኪ የእምነቱ ተከታዮች ህፃናት ልጆች በተወለዱ በጥቂት ቀናት እንዲያስገርዙ የሃይማኖቱ መሪዎች ዘወትር እንደሚሰብኩ አስታውሰው ይህ ደግሞ በጀርመን ህገ ወጥ ሆኖ ከተከለከለ ልጆቻቸውን ለማስገረዝ ድርጊቱ ህጋዊ ወደ ሆነባቸው አገሮች ለመሄድ መገዳደቸው አይቀርም ይህ ደግሞ ለእምነቱ ተከታዮችም ሆነ ለሃይማኖት አባቶች አስቸጋሪ ነው ይላሉ ። ግርዛት እዚህ መከልከሉ ደግሞ ይላሉ ዶክተር ሞግሃደም ሌሎች መዘዞችን ማስከተሉ አይቀርም
«የኮሎኙ ብይን የሚያስከትለው አደጋ ምናልባት ሃይማኖታዊ ግርዘት ለሚያከናውኑ ወገኖች ከመደበኛ ክሊኒኮች ውጭ ጥራትም ሆነ ንፅህናው ያን ያህል ባልተሟላ ቦታ ተግባራዊ እንዲያደርጉ የሚገፋፋ መሆን መቻሉ ነው ። እዚህ ላይ እኔ የምሰጋው እርስ በርሱ የሚቃረን ሁኔታ እንዳይፈጠር ነው ። ጉዳዩ የሚመለከታቸው ልጆች የጤንነት አጠባበቅ ደረጃ በብይኑ ምክንያት ከመሻሻል ይልቅ እንዳይባባስ ያሰጋል ። »
ዶክተር ሞግሃደም ወላጆች ልጆቻቸውን ማስገረዛቸው ልጅን የማሳደግ መብታቸውን አለአግባብ መጠቀም ማለት እንዳይደለም ያስረዳሉ ። በአሁኑ ጌዚ ትኩረት የተሰጠው በልጃገረዶች ላይ የሚፈፀመው ግርዘት ያለ አንዳች ማመንታት እንዲከለከል መደረጉ ነው ። አንዳንዶች አስተያየት ሰጭዎች አሁን የተከሰተውን ችግር ለማስቀረት በጀርመን በህግ አንድ አዲስ አንቀፅ መከታቱ ይጠቅማል ይላሉ ። ማርቲን ቦዘ ግን በሃይማኖት ሳቢያ ወንዶች ልጆች እንዲገረዙ የማይከለክ ልዩ የሆነ የህግ አንቀፅ ይፈቀድ መባሉን ይህን ያህል የሚሰምር ሆኖ አይታያቸውም
« የልጃገረዶችን ግርዘት የማዋለጃ አካልን ክፉኛ በመጉዳት የሚከናወን ተግባርን በቀጥታ የሚፃረር ረቂቅ ህግ ቀርቧል የዚህም ረቂቅ ህግ ዋና ትኩረት የእንዲህ ዓይነቱን አካልን የመተልተል እርምጃ በአንፃሩ የሚያስቀር ነው ። ሃይማኖታዊ ልምዶችን መሠረት ያደረገና ለይቶ የሚተውና ከቅጣት ነፃ የሚያደርግ መመሪያ ይውጣ ከተባለ ደንቡ ወደፊት ምን መዘዝ እንደሚያስከትል ለማወቅ ያዳግታል ። »
ሂሩት መለሰ