አንጎላ እና አዲሱ አከራካሪ ህገ መንግስት
ቅዳሜ፣ ጥር 15 2002ማስታወቂያ
አንጎላን ካለፉት ሰላሳ ዓመታት ወዲህ የሚመሩት ፕሬዚደንት ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶሽ በዚሁ አሰራር የተካኑ ፖለቲከኛ ናቸው። እአአ በ 1992 ዓም ብቻ ነበር ራሳቸውን ለምርጫ በተወዳዳሪነት ያቀረቡት። ግን ያኔ፡ እንደሚታወሰው፡ የእርስበርሱ ጦርነት እንደገና በመፋፋሙ የመጀመሪያው ዙር ምርጫ ብቻ ነበር የተካሄደው። እአአ ከ 2002 ዓም ወዲህ አንጎላ ውስት ሰላም ሰፍኖዋል፤ እና አንጎላ ዜጎች ከዚያን ጊዜ ጀምረው ቃል የተገባላቸው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሚደረግበትን ቀን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። ፕሬዚደንቱ ግን ምርጫ ለማካሄድ ፍጹም ሀሳብ የሌላቸው ከመሆኑም ሌላ፡ የህዝቡ ትኩረት በበሀገሩ በሚካሄደው የእግር ኳስ ዋንጫ ግጥሚያ ላያ ያረፈበትን ሁኔታ ከለላ በማድረግ ስልጣናቸውን ማራዘም የሚችሉበትን አንቀጽ በህገ መንግስቱ ለማስፈር ሙከራ ይዘዋል።
አርያም አብርሃ/ዩሀንስ ቤክ