«አንድ ላፕቶፕ ለእያንዳንዱ ልጅ፣»
ረቡዕ፣ ኅዳር 5 2005ማስታወቂያ
በተቀላጠፈ ሁኔታ የተለያዩ አስደናቂ ተግባራትንም ሊያከናውኑ ይችላሉ። በአሁኑ ጊዜ ከ 85 ሚሊዮን ያላነሰ ህዝብ እንዳላት የሚነገርላት ኢትዮጵያ፣ 16 ሚሊዮን ያህል ዕድሜያቸው በ 6 እና 14 ዓመት መካከል የሚገመት 16 ሚሊዮን ያህል የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንዳሏት ይገመታል። የትምህርት ዕድል ያላገኙት እጅግ በዛ ያሉ መሆናቸው የሚያጠራጥር አይደለም።
በዓለም ዙሪያ ድህነትን ለመቅረፍ፣ ብሎም ለማስወገድ አንዱ አብነት ፣ ትምህርት መሆኑን ጠበብት ይስማሙበታል። ስለሆነም በዚህ ረገድ ፣ አንዳንድ የበለጸጉ ሃገራት መንግሥታት ብቻ ሳይሆኑ የመንግሥት ያልሆኑ ድርቶችም ጠቃሚ ድርሻ ሊያበረክቱ እንደሚችሉ እሙን ነው።
ተክሌ የኋላ፣
ነጋሽ መሐመድ