«አናሎግ» ና «ዲጂታል»
ሐሙስ፣ የካቲት 12 2007NTV KTN «ሲቲዘን TV» እና QTV በሚሉ ምሕጻረ ቃላት የታወቁት ዐራት የቴሌቭዥን ተቋማት የተናደዱት፣ «ትንሽ የመዘጋጂያ ጊዜ ሳይሰጠን »በማለት እንጂ ዘመናዊ ወደሚሰኘው የዲጂታል አቅድ ሽግግር መደረጉን በመሠረተ ሐሳብ ተቃውመው አይደለም። የዛሬው ሳይንስና ሕብረተሰብ ፤ ቅንብር ስለ አናሎግና ዲጂታል ምንነት የአንድን ባለሙያ ትንተና ያቀርባል።
ወደ ቴክኒኩ ዓይነት ስንመለስ ፣ ሽግግር የተደረገው «አናሎግ » ከሚሰኘው ወደ «ዲጂታል» ነውና ፤ አናሎግ ምንድን ነው ዲጂታልስ? በዩናይትድ ስቴትስ ፤ ሜሪላንድ ፌደራል ክፍለ ሀገር ሐዎርድ ማሕበረሰባዊ ኮሌጅ ፤ የኮምፒዩተር መረብ (ኔትወርክ) ና የኢንተርኔት ደኅንነት ጥበቃ ጉዳይ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር መንግሥቱ አዱኛ እንዲህ ያብራራሉ።
አምና የህዝቧ ቁጥር 45,941,977 መድረሱ በተነገረላት ኬንያ፤ ከ 90 በላይ በመካከለኛ ሞገድ የሚሠሩ ራዲዮ ጣቢያዎች ፣ 15 ያህል የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ይገኛሉ። የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚው ህዝቧ መጠን 32,2 ሚሊዮን ገደማ ሲደርስ በኢንተርኔት የሚገለገለውም ከ 19 ,6 ሚሊዮን በላይ መሆኑ ነው የሚነገረው ። በመገናና ብዙኀን ሰፋ ያለ አገልግሎት የምታገኘው ሀገር ናት እንግዲህ በ«አናሎግ » ከማሠራጫ ደንብ ወደ ዲጂታል ሥርዓት የተሸጋገረችው። ዲጂታል ምንድን ነው ? ዶ/ር መንግሥቱ አዱኛ--
ተክሌ የኋላ
ሸዋዬ ለገሠ