አነጋጋሪው የፕሬዚዳንት ዑመር አልበሽር ጉብኝት
ቅዳሜ፣ መጋቢት 19 2001ማስታወቂያ
አልበሽር በሰሩት ወንጀል ተይዘው ለፍርድ ይቅረቡ ሲል ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት የእስር ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወቃል። ሁኔታው ታዲያ ዓለምን በሶስት የከፈለ ይመስላል። ገሚሱ ውሳኔው ተገቢ ነው፤ ፕሬዚዳንቱ ውለው ሳያድሩ ለፍርድ ይቅረቡ ሲል፤ ሌላው ደግሞ፤ የለም! የአንዲት ሉዓላዊት ሀገር መሪ በስልጣን እያሉ መክሰስ ፍትሀዊ አይደለም ሲል ተደምጧል። ቀሪው አካል ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ ማለት ነው አስተያየት ከመስጠት የተቆጠበ ይመስላል።
ታደሰ እንግዳው
ማንተጋፍቶት ስለሺ