የተተቸው የኢሕአዴግ መግለጫ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 24 2010ማስታወቂያ
የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መግለጫ ፓርቲው ከዚህ ቀደም ከሚያወጣቸው መግለጫዎች የተለየ ነገር ይዞ አልመጣም የሚሉ አሉ፡፡ በመግለጫው የተነሱ ጉዳዮች “ሾላ በድፍን” መሆናቸውን እና ለህዝብ በሚገባ መልኩ ተብራርተው አለመጻፋቸውን የተቹም በርካቶች ናቸው፡፡
የዋሽንግተኑ ወኪላችን ናትናኤል ወልዴ ኗሪነታቸውን በአሜሪካ ያደረጉ የፖለቲካ አራማጆች እና ታዛቢዎችን አነጋግሯል፡፡ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) ዋና ዳይሬክተር ጀዋር መሐመድ፤ በኢሊኖይ ግዛት የሀርፐር ኮሌጅ ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው እና የህግ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ብርሃነመስቀል አበበ ሰኚ አስተያየታቸውን ለዶይቸ ቬለ አካፍለዋል፡፡ ዝርዝር ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ናትናኤል ወልዴ
ሸዋዬ ለገሠ