አነጋጋሪው አዲሱ የብሪታኒያ የኢሚግሬሽን ህግ
ረቡዕ፣ ሰኔ 5 2005ማስታወቂያ
የብሪታኒያ መንግሥት ከአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ውጭ የሚገኙ ቤተሰቦቻቸውን ወደ ብሪታኒያ ለማምጣት ለሚፈልጉ የብሪታኒያ ዜጎች ያወጣው አዲስ ህግ እያነጋገረ ነው ። አዲሱ ህግ ዜጎች ፣ ባለቤቶቻቸውን ወደ ብሪታኒያ ለማስገባት የዓመት ገቢያቸው ቢያንስ 18 600 ፓውንድ እንዲሆን ደንግጓል ። በአዲሱ ህግ መሰረት ልጆቻቸውን ማስመጣት የሚፈልጉ ዜጎች ደግሞ በ ልጆች ቁጥር የሚጨምር በህጉ የተደነገገው ዓመታዊ ገቢ ማሳየት ይኖርባቸዋል ። ህጉ ቤተሰብ የሚለያይ ና ቤተሰብ የመመስረት መብትን የሚጋፋ ነው ሲሉ የመብት ተሟጋቾች አጥብቀው ተቃውመውታል ። የብሪታኒያ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዚህ ህግ ተጎጂ መሆናቸውን የለንደኗ ወኪላችን የሃና ደምሴ ዘገባ ያስረዳል።
ሃና ደምሴ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ
ሃና ደምሴ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ