አቶ በቀለ ነጋ ቁም እስር ላይ ናቸው
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 21 2008ማስታወቂያ
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ በምኅፃሩ (ኦፌኮ) ዋና ጸሓፊ አቶ በቀለ ነጋ ደግሞ ዛሬ የእጅ ስልካቸው ተቀምቶ በቁም እስር እንደሚገኙም ተገልጧል። አቶ በቀለ ገርባ በጠና ታመዋል፤ ህክምናም ተከልክለዋል መባሉን በተመለከተ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ዛሬ በስልክ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ከቤተሰባቸውም ሆነ ከማንኛውም ሰው ጋር እንዳይገናኙ መከልከላቸውን ጠቅሰዋል። የኦፌኮ ዋና ጸሓፊ አቶ በቀለ ነጋ ደግሞ ዛሬ ጠዋት ስላካቸው ተቀምቶ «በቁም እስረኝነት» እንደሚገኙ ተገልጧል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ