አተት በትግራይ እና በአማራ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 11 2008ማስታወቂያ
በትግራይ እና በአማራ ክልሎች አጣዳፊ ተቅማጥ እና ተውከት በምህፃሩ አተት በሰዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የጤና ባለሞያዎች አስታወቁ ።የመቀሌ ሆስፒታል በበሽታው ለተያዙ የተለየ ቦታ ከልሎ የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን ገልጿል ።ከዚሁ ጋር ሆስፒታሉ ስለ በሽታው ምንነት ስለ ሚተላለፍባቸው መንገዶች እና ስለ መከላከያው የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምሕርት በመስጠትም ላይ መሆኑን አስታውቋል ። በትግራይ በአተት መንስኤ የሞተ አለ እየተባለ ቢነገርም የክልሉ የጤና ቢሮ ግን ይህን አስተባብሏል ። አተት ከመቀሌ ሌላ በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች መከሰቱም ተነግሯል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ