አብን አባላት እና ደጋፊዎቹ መታሠራቸውን ማመልከተ
ዓርብ፣ ሰኔ 21 2011ማስታወቂያ
የፖርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ እንዳሉት ግለሰቦቹ እየተያዙ ያሉት መፈንቅለ መንግስቱን በማቀናበር አብን አለበት በሚልና ፣ የገንዘብ ድጋፍ ታደርጋላችሁ በሚል መታሰራቸውን ፤ አንዳንዶቹም የት እንደታሰሩ እንደማይታወቅ ተናግረዋል።
ጉዳዩ ህዝብን ወደ አለመረጋጋት፣ ሀገሪቱንም ወደባሰ ሁኔታ የሚያስገባ በመሆኑ ድርጊቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ፣ የተያዙትም እንዲለቀቁ ጠይቋል። ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ጉዳዩን ለህዝብ በማሳወቅ ህዝቡ በመንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድር እናደርጋለን ሲሉ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ለ DW ተናግረዋል። መንግሥት ከዚሁ የመፈንቅለ መንግሥት ተግባር ካለው ጉዳይ ጋር በተያያዘ ትናንት ስድስት ሰዎችን በሽብር ከስሶ ፍርድ ቤት ማቅረቡን መዘገባችን ይታወሳል። ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዘገባ ልኮልናል።
ሰሎሞን ሙጬ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ