አበሻ ኤጀንሲ ሊቢያ የሚገኙ ስደተኞች ና UNHCR
ሐሙስ፣ መጋቢት 22 2003ሊቢያ ከነበሩት ኢትዮጵያውያን ኤርትራውያንና የሶማሌ ስደተኞች ውስጥ የተወሰኑት ግን አበሻ ኤጀንሲ በተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅት ድጋፍ በልዩ ልዩ ጊዜያት ወደ ኢጣልያ መግባት ችለዋል ። በዚህ ድርጅት እገዛ እና ማሳሰቢያ ከሊቢያ ግጭት በኋላ 110 ሰዎች በአየር ወደ 1500 ደግሞ በባህር ኢጣልያ መግባት መቻላቸውን የድርጅቱ ሃላፊና መሥራች አባ ሙሴ ዘራይ ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ። ከሊቢያ የተለያዩ ከተሞች መውጣት ስለተሳናቸው ሌሎች ስደተኞች እና ድርጅታቸው ስለሚያደርግላቸው እገዛ አባ ሙሴን በስልክ ጠይቄያቸዋለሁ ። ተሳክቶላቸው ኢጣልያ መግባት የቻሉት ስደተኞች በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ በቅድሚያ ይገልፁልናል ። የሊቢያ ስደተኞችና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የሊቢያው ጦርነትና በዚያ የሚገኙ ስደተኞች ሁኔታ አሁንም እንዳነጋገረ ነው ። ብራሰልስ ቤልጅየም በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የአውሮፓ ህብረት የስደተኞች መልሶ ማቋቋም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን በታሰበበት በትናንትናው ዕለት በሊቢያ የሚገኙ ስደተኞች ጉዳይ ተነስቶ ነበር ። የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ በዚሁ ስብሰባ ላይ የተገኙትን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን UNHCR እና በአውሮፓ ህብረት የአሜሪካን የስደተኞች ጉዳይ ተወካይን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራል ።
ገበያው ንጉሤ
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ