1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሶሳን ከመተከል የሚያገናኘዉ ድልድይ አገልግሎት ማቋረጡ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 9 2012

አሶሳን ከመተከል ዞን የሚያገናኝ በአባይ ወንዝ ላይ የተሰራው ድልድይ በውኃ በመሞላቱ የህዝብ ማመላለሻ  መኪኖች በሌላ አማራጭ መንገድ መጠቀም ከጀመሩ ዛሬ አምስተኛ ቀናቸው ነው፡፡ በውኃ ተሞላ የተባለው ድልድይ ከግድቡ በላይ በኩል ሆኖ  20 ኪ.ሜ  ከግድቡ ይርቃል ተብለዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3fRVI
Äthiopien Luftbild Grand-Ethiopian-Renaissance-Talsperre
ምስል DW/Negassa Desalegen

አሶሳን ከመተከል ዞን የሚያገናኝ በአባይ ወንዝ ላይ የተሰራው ድልድይ በውኃ በመሞላቱ የህዝብ ማመላለሻ  መኪኖች በሌላ አማራጭ መንገድ መጠቀም ከጀመሩ ዛሬ አምስተኛ ቀናቸው ነው፡፡ በውኃ ተሞላ የተባለው ድልድይ ከግድቡ በላይ በኩል ሆኖ  20 ኪ.ሜ  ከግድቡ ይርቃል ተብለዋል፡፡ የዛሬ አስር ዓመት በቻይና የተገነባውና 500 ሜትር ያህል ርዝመት ያለው ድልድይ እስካሁን በክረምት ወራት ውኃ ሙላት ተሸፍነው አያውቅም ይላሉ በመተከል ዞን የዘመን ባስ ስምርት ተቆጣጣሪዎች እና ባለንብረቶች፡፡ ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ወደ አሶሳ የሚመጡ መኪኖች በግድቡ በታች በኩል ከዚህ በፊት በተሰራው አማራጭ መንገድ እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ የግድቡን የመጀመሪያ ምዕራፍ የውኃ ሙሌት ለማከናወን የሚያስችል ዕቅድ 560 የከፍታ መጠኑን መከናወኑን ከሳምንት በፊት ጠቅላይ ሚንስተር ዐቢይ አህመድ በፓርላማ ላይ ተናግረዋል፡፡ የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስተር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለም ግድቡ ውኃ መያዝ መጀመሩን ትናንት ለመገናኛ ብዙሐን በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡አቶ ማሞ አያና የዘመን ባስ ስምሪት ኃላፊ ሲሆኑ መተከን ዞንን ከአሶሳ ጋር የሚያገናኝ መንገድ ባለፈው ሳምንት በውኃ መሸፈኑን ተናግረዋል፡፡ ይህ በውኃ የተሸፈነው መንገድ በተለይ መተከል ዞንን ከአሶሳ ዞን ጋር የሚያገናኝ አባይ ወንዝ ላይ የተሰራው ትልቁ ድልድይ  በውኃ የተሞላ ሲሆን ተጨማሪ 80 ኪ.ሜትሮችን በመዞር ከግድቡ በታች በኩል በማንኩሽ ከተማ  አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በክረምት ወራት አካባቢው አሁን ባለው መልክ በውኃ ሲሞላ የመጀመሪያ መሆኑን የተናሩ ሲሆን አካባቢው በውኃ መሸፈን ከታላቁ ህዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችልም ያላቸውን ግምት ገልጸዋል፡፡ 
የአካባቢው በውኃ መሸፈን ከአባይ ግድብ ውኃ ሙሌት ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ ከመንግስት አካላት ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡ የታላቁ የኢትዩጵ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ጋር የተገናኘ ስለመሆኑ የጠየቅናቸው በየደረጃው ያሉት የስራ ኃላፊዎች  በግልጽ መናገር አልፈለጉም፡፡ በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ  የግድቡን የግንባታ ሂዴት አስመልክቶ የግድቡ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ በሰጡን ሀሳብ የግደቡ የውኃ ሙሌት የመጀመሪያ ምዕራፍ ለማከናወን የግድቡ የከፍታ መጠን 560 ሲደርስ  መሆኑን ገልጸው ነበር፡፡ የመጀመሪያውን ምዕራፍ የውኃ መሌት ለመጀመር  እና ሁለት የተርባይን ጀነሬተሮችን በመጠቀም በቀጣይ ዓመት ኤሌክትሪክ ለማመንጨት የሚያስችል ዕቅድ ይዘው እየሰሩ እንደሚገኙ በወቅቱ ተናግረዋል፡፡
ከሳምንት በፊት ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር ዐቢይ ዐህመድ በህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ስለ ታላቁ ህዳሴ ግድብ በሠጡት ማብራሪያም የግድቡ ከፍታ 525 ላይ እንደነበርና በአሁኑ ጊዜ ደግሞ በግንባታው ሂዴት የነበሩትን ውስብስብ ችግሮችን በመቅረፍ የከፍታ መጠኑን 560 ላይ ማድረሳቸውን አብራርተዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት በውኃ ተሞላ የተባለውን ድልድልን ጨምሮ ግድቡ ሲጠናቀቅ አካባቢው በውኃ እንደሚሸፈን ታሳቢ ተደርጎ ከሁለት ዓመት በፊት ከግድቡ በታች በኩል  አሶሳን ከመተከል ዞን እና  ሌሎችም አካባቢዎች ጋር ሚያገናኝ አማራጭ መንገድ በሳሊኒ ኩባንያ ተሰርቶ የነበረ ሲሆን ከባለፈው ቅዳሜ አንስቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡፡ መንገዱም ከአሶሳ መተከል ለመድረስ ከዚህ ቀደም 378 ኪሜትር የነበረው ሲሆን በአድሱ መንገድ ደግሞ 449  ያህል ኪ.ሜ ይርቃል ተብሏል፡፡


ነጋሳ ደሳለኝ 


አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ