አሳድና ምዕራቡ ዓለም
ዓርብ፣ ነሐሴ 13 2003ማስታወቂያ
ዛሬም በአገሪቱ ከዓርቡ ጸሎት ቀጥሎ የተካሄደዉን የተቃዉሞ ሰልፍ ለመበተን የመንግስት ኃይሎች ጥይት የተኮሱ ሲሆን የ15 ሰዎችን ህይወት እንዳጠፉ የመብት ተቆርቋሪዎች አመልክተዋል። አልአሳድ ለተመድ ዋና ጸሐፊ ባን ጊ ሙን ከእንግዲህ የኃይል ርምጃ እንደማይወስዱ ቢገልፁም ቃላቸዉን አለማክበራቸዉ ነቀፌታዉን አጠናክሮታል። አሜሪካን ስልጣን እንዲለቁ ትናንት ስትጠይቅ፤ የአዉሮጳ ኅብረትም ተከትሏታል። ቻይናና ሩሲያ ግን አሁንም አሳድ ማስተካከያ እስኪያደርጉ ፋታ ያግኙ ባይናቸዉ።
ነብዩ ሲራክ
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ