ኔልሰን ማንዴላ : የነፃነት ድምፅ
ኔልሰን ማንዴላ የቆሙት ለአዲሲቷ ደቡብ አፍሪቃ- ለዓለም ዓቀፍ መቻቻል እና ነፃነት ነበር
ደህና ሁኑ ኔልሰን ማንዴላ
በብዙ ደቡብ አፍሪውያን የሚያስታዉሱት ፈገግታ። የጎሳቸዉ ሰዎች በፍቅር በጡዎሳ «ማዲባ» ሲሉ ይጠሩዋቸዋል። ማንዴላ በመላዉ ዓለም የአዲሲቷን ደቡብ አፍሪቃ ነፃነትና መቻቻል ይወክላሉ።
የጥቁሮች ጠበቃ
ኔልሰን ሮሊህላህላ ማንዴላ እጎአ ሐምሌ 18 ቀን 1918ዓም በደቡብ አፍሪቃይቷ ምስራቅ ኬፕታዉን ተወለዱ። የ 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁም ህግ አጠኑ። በትምህርት ላይ ሳሉም በፖለቲካዉ እየተሳተፉ የነጭ ዘረኝነትን መታገል ጀመሩ። እጎአ 1952 ዓም በሀገሪቷ በጥቁሮች እጅ በነበረው የጠበቆች መስሪያ ቤት መስራት ጀመሩ። መስሪያ ቤቱም ከስምንት ዓመት በኋላ ሙሉ በሙሉ ተቃጥሎ ወደመ።
የነጭ ዘረኝነት
የነጭ ዘረኝነት- በደቡብ አፍሪቃ የነበረውን የጥቁሮች እና የነጮች ልዩነት ማንዴላ ገና በልጅነታቸው እና በወጣትነት እድሜያቸው አልፈዉበታል። አባታቸው የጡዎሳ ስም አወጡላቸው፤ ሮሊህላህላ ሲሉ በቀጥታ ሲተረጎም «ቅርንጫፎች ሰባሪው» እንደማለት ነው። በፈሊጣዊ አነጋገር ደግሞ «አመፅ ጫሪው»።
ቦክሰኛው ማንዴላ
በወጣትነት እድሜያቸው ማንዴላ ቦክስ ከሚያስደስታቸው ስፖርት አንዱ ነበር። «በቦክስ መድረክ ላይ ስልጣን፣ እድሜ፣ የቆዳ ቀለም እና ሀብት ቦታ የላቸውም» ሲሉ ነበር ለስፖርቱ ያላቸውን ፍቅር የገለፁት። ማንዴላ ወህኒ ቤት በነበሩበት ጊዜም ከስፖርት አልተለዩም። ክብደት ማንሳት፤ የትከሻና ደረት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የየዕለት ተግባራቸዉ ነበር።
የእድሜ ልክ እስራት ብይን
እጎአ 1964 ዓም ፦ የኔልሰን ማንዴላ እና ሌሎች የፀረ አፓርታይድ ታጋዮች ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ለመታዘብ ከፊት ለፊት የተሰበሰበውን ሰው ፖሊስ ይበታትን ነበር። ሪቮኒያ በተሰኘው የክስ ሂደትም ኔልሰን ማንዴላ ለፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው የእድሜ ልክ እስራት ተመየነባቸው።
አስርት ዓመታት በወህኒ ቤት
በ5 ስኩየር ሜትር የተወሰነች ህይወት፤ በዚህች ጠባብ ክፍል ውስጥ ማንዴላ ከ27ቱ የእስር አመታቸው 18ቱን አሳልፈዋል። 46664 የእስር ቤት መለያ ቁጥራቸው ነበር። « የምታወቀዉ በቁጥር ነበር» ነው ያሉት ማንዴላ ከስር ከተለቀቁ በኋላ።
ትግሉ ቀጠለ
ኔልሰን ማንዴላ ወህኒ ቤት ሳሉ ሌሎች የነፃነት ተሟጋቾች ትግሉን ቀጠሉ። በተለይ የያኔው ባለቤታቸው ዊኒ ማንዴላ (ፎቶዉ ላይ መካከል ያሉት): በጥቂት ነጮች አመራር ስር የነበረውን መንግስት ከሚቃወሙት ግንባር ቀደም ነበሩ።
ዓለም ተሳተፈ ...
የደቡብ አፍሪቃን እጣ ፈንታ፤ በለንደን ዌምብሊ ስታዲየም እኤአ1988 ለኔልሰን ማንዴላ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ድግስ ተዘጋጀ። በዓለም ታዋቂ የሆኑ አርቲስቶች ተገኝተው የማንዴላን 7oኛ ዓመት ልደት አከበሩ። የነጭ ዘረኝነትንም ተቃወሙ። ወደሰባ ሺ የሚገመቱ በስታዲዮሞ ተገኝተዉ ወደመቶሺ ገደማ ደግሞ በቴሌቪዥን 10 ሰዓት የፈጀውን የሙዚቃ ድግስ ተከታተሉ። ክስተቱም በ60 ሀገራት በቀጥታ በቴሌቪዥን ተላልፏል።
በመጨረሻም ነፃ
ከ27 ዓመት በኋላ ማንዴላ እጎአ የካቲት 11ቀን 1990 ከስር ተለቀቁ። እሳቸው እና የቀድሞ ባለቤታቸው ዊኒ ማንዴላ እጃቸውን ወደ ሰማይ አንስተው ጥቁሮችን ከነጮች ዘገኛና የበላይነት አገዛዝ ነፃ ያወጡበትን ቀን በአንድነት አከበሩ።
ዳግም ወደ ፖለቲካው መድረክ
ወደ ብሔራዊ የአፍሪቃ ብሔራዊ ሸንጎ (ANC) ተመልሰው ማንዴላ እጎአ ግንቦት 1990 ከወቅቱ የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚዳንት ፍሬደሪክ ደ ክሌሬክ ጋ እንዴት ደቡብ አፍሪቃ ያለ ነጭ ዘረኝነት በጋራ መራመድ እንደምትችል ተወያዩ። ለዚህም ሁለቱም የቀድሞ የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚዳንቶች የዓለም የሰላም ኖቢል ተሸለሙ።
አጋሮች
ኦሊቨር ታምቦ (በግራ በኩል)እና ዋልተር ሲሱሉ (በስተ ቀኝ) የሟንዴላ የረጅም ጊዜ አጋሮች ናቸው። እጎአ 1944 እነሱና ሌሎች በአንድነት የአፍሪቃ ብሔራዊ ሸንጎ የወጣቶች ክንፍን መስርተው ትልቅ የፀረ አፓርታይድ አመፅ አካሄዱ። ሲሱሉ እንደ ማንዴላ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸዉ። ታምቦ 30 ዓመታት በስደት፤ አብዛኛዉን ጊዜም ለንደን አሳለፉ። ከ1990 በኋላ ሁሉም በANC የኃላፊነት ቦታ ያገለግሉ ጀመር።
የፕሬዚዳንትነት ቃለ መሀላ
እጎአ ግንቦት 10 1994 በደቡብ አፍሪቃ ታሪክ ተሰራ። ከመጀመሪያው ነፃ ምርጫ በኋላ ማንዴላ የመጀመሪያው የሀገሪቱ ጥቁር መሪ ሆነው ተመረጡ። 1999ኝም ዳግም ቢመረጥሙ ስልጣናቸዉን ለፖለቲካ ደቀመዝሙራቸዉ ታቦ ምቤኪ አስረከቡ።
ከበቀል ይልቅ እርቅ
ማንዴላ በአፓርታይድ ዘመን የተፈፀመውን ወንጀል ለማጣራት እጎአ 1996 «የእውነታ እና የብሄራዊ እርቅ ምክር ቤትን» መሰረቱ። ሊቀመንበሩም የደቡብ አፍሪቃ ሊቀጳጳስ እና ኋላም የሰላም የኖቢል ተሸላሚ የሆኑት ዶስሞንድ ቱቱ ናቸው። የምክር ቤቱም ስራ ትችት አልቀረለትም። በርካታ ተበዳዮች ጥፋተኞች ድርጊታቸዉን በአደባባይ ስላመኑ ብቻ አለመቀጣታቸዉን አልወደዱትም።
2010 የዓለም ዋንጫ ውድድር ዝግጅት
እጎአ ግንቦት 15 2004 ደቡብ አፍሪቃ የ2010ርን የዓለም ዋንጫ ለማዘጋጀት ተመረጠች። ማንዴላም በደስታ ዋንጫውን ታቅፈው ለትልቁ የስፖርት ዝግጅት ጨፈሩ። ሕዝቡም በደስታ ፈነደቀ። የአለም ዋንጫ በአፍሪቃ ሲካሄድም የደቡብ አፍሪቃው የመጀመሪያው ነዉ።
በቀስደመናዉ አገር ጥላ
እጎአ 2008 ዓም በበርካታ የሀገሪቱ ትልቅ ከተሞች በሚገኙ ጎስቋላ መንደሮች ትልቅ አመፅና ብጥብጥ ተካሄደ። ስደተኞች ላይ ባነጣጠረዉ የጭካኔ ርምጃ ብዙዎች ተገደሉ። በርካቶችም በመገረም ማንዴላ የመሰረቷት ቀስተዳመና አገር ሰላም እና ተቻችሎ መኖር አበቃለት እንዴ ሲሉ በመገረም ጠየቁ?
የመጨረሻዎቹ ዓመታት
በመጨረሻዎቹ የኑሮ ዘመናቸው ማንዴላ ራሳቸውን ከአደባባይ ማግለል ጀመሩ። አብዛኛዉን ጊዜያቸውንም ከቤተሰቦቻቸው ጋ ማሳለፉን መረጡ። ከ2 ዓመት በፊት ማንዴላ የ93ኛ ዓመት የልደት በዓላቸዉን ከልጅ ልጅ እና ከልጅ ልጅ ልጃቻቸው ጋ እንዲህ አከበሩ።