ናይጀሪያ፡ ካሜሩንና የባካሲ ርክክብ8 ነሐሴ 2000ሐሙስ፣ ነሐሴ 8 2000ናይጀሪያ በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገውን የባካሲ ልሳነ ምድር ዛሬ ለካሜሩን አስረክባለች።https://p.dw.com/p/ExeAየባካሲ ልሳነ ምድርምስል APማስታወቂያርክክቡን የሚቃወሙ ወገኖች ስነ ስርዓቱን እንዳያጨናግፉ ስጋት በመፍጠሩ በትልቁ የባካሲ ልሳነ ምድር የአባና ከተማ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው የሰንደቅ ዓላማ ሰቀላው ስነ ስርዓት በጸጥታ ስጋት የተነሳ ከከተማይቱ አንድ መቶ ዘጠና ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደምትገኘው ወደካላባር ከተማ ተዛውሮዋል። በዚሁ ስነ ስርዓት የተሳተፉት የተመድ ዋና ጸሀፊ ፓን ኪ ሙን ርክክቡን ታሪካዊ ሲሉ አሞግሰዋል።