1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቻይና፤ የግብፅና የቱኒዚያ ንቅናቄ አስግቷታል

ረቡዕ፣ የካቲት 9 2003

ህዝባዊ አመጽ በግብፅና ቱኒዚያ ከተቀጣጠለበት ጊዜ አንስቶ ሁኔታዎች በቻይናም ሊገነፍሉ የደረሱ ይመስላል። አንድ ቻይናዊ ፖለቲከኛ ነገሮች በኛም ሀገር በቋፍ ላይ ነው ያሉት ሲሉ ገልፀዋል። በእርግጥ በግብፅና ቱኒዚያ የተከናወነው አይነት ህዝባዊ አመፅ በቻይናም ቢቀጣጠል ምን ይከሰት ይሆን?

https://p.dw.com/p/R1HB
የቻይና ወታደሮች በቲየን አን ሜን አደባባይ
የቻይና ወታደሮች በቲየን አን ሜን አደባባይምስል AP

በእርግጥ ለቻይናውያኑ በግብፅና በቱኒዚያ የተቀጣጠሉት ህዝባዊ አመፆች አዲስ አይደሉም። ቻይናውያን ከፍተኛ መስዋዕት ያስከፈላቸውን ታላቅ ንቅናቄ የዛሬ 22 ዓመታት ግድም እዛው ቻይና ውስጥ ፈፅመውታልና። ያኔ ኮሚኒስት መራሹ የቻይና መንግስት ሰላማዊ ሰልፈኞቹን በጅምላ ነው የጨረሰው። እንደ ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ገለፃ ከሆነ፤ በወቅቱ ቻይና ውስጥ 3000 ሰዎች በንቅናቄው ሂደት ተገድለዋል። ያን እልቂት ብዙዎች ዛሬም ድረስ የ«ቲየን አን ሜን ፍጅት» በማለት ያስውሱታል። ከቲየን አን ሜኑ ፍጅት በኋላ ግን ቻይናውያን በፍርሀት ተሸብበው አልተቀመጡም። ዛሬ ልክ እንደ ግብፃውያኑና ቱኒዚያውያኑ ሁሉ ኢንተርኔትን በመጠቀም በከፍተኛ ሁኔታ እየተወያዩ ነው።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ