ትኩረት ለአፍሪቃ የትምህርት ጥራት
ዓርብ፣ ግንቦት 26 2008ማስታወቂያ
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአፍሪቃ ህፃናት ትምህርት ቤት አይሄዱም ። የትምህርት እድል ከሚያገኙት አብዛኛዎቹም በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ይገደዳሉ ። ከዚህ ሌላ በክፍለ ዓለሙ የሚሰጠውም ትምህርት ቢሆን ጥራቱ እያስሽቆለቆለ መሄዱ አብይ ችግር መሆኑ ይወሳል ። በአፍሪቃ ከጊዜ ወደ ጊዜ ደረጃው ዝቅ እያለ ነው የሚባለው የትምህርት ጥራት ትኩረት እንዲሰጠው የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ በዚህ ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደ ስብሰባ ላይ አሳስቧል ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዝርዝሩን አዘጋጅቷል ።
ጌታቸው ተድላ ኅይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ