ቱስክ፤ ብሪታንያ ከኅብረቱ የምትወጣበት ቀነ ቀጠሮ ይራዘም
ረቡዕ፣ መጋቢት 18 2011ማስታወቂያ
የአዉሮጳ ኅብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ቱስክ፤ ለኅብረቱ ፓርላማ ላይ ባደረጉት ንግግር ብሪታንያ ከአዉሮጳ የምትወጣበት ቀነ ቀጠሮ እንዲራዘም አስታወቁ። ቱስክ በንግግራቸዉ የብሪታንያን ከአዉሮጳ ኅብረት መዉጣት የሚቃወሙና፤ ሁለተኛ ሕዝበ ዉሳኔ እንዲካሄድ ጥያቄ የሚያቀርቡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የብሪታንያ ዜጎችን ቸል ማለት አይቻልም ሲሉ ለፓርላማዉ አባላት ተናግረዋል። ኅብረቱ ብሪታንያ ከአዉሮጳ ኅብረት የምትወጣበትን እስከ ሚያዝያ 4 ድረስ ማራዘሙ ይታወቃል። ዛሬ ምሽት ላይ የብሪታንያ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት በብሪግዚት ዉል ላይ ድምፅ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። እስካሁን በተሰበሰቡ የቅድምያ መዘርዝር መረጃዎች መሰረት መወሰኛ ምክር ቤቱ አብላጫ ድምፅ ላይሰጥበት ይችላል ተብሎአል። የፊታችን አርብ ብሪታንያ ከየአዉሮጳ ኅብረት አባልነት ትወጣለች ተብሎ የተያዘዉ የመጀመርያ ቀነ-ቀጠሮ ነዉ።
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሠ