ቱርክ የአውሮፓ ኅብረትና የሶርያ የተኩስ አቁም ሀሳብ
ሰኞ፣ የካቲት 7 2008ማስታወቂያ
የፕሬዚዳንት አሳድ ወታደሮች በሩስያ ጦር አዉሮፕላኖች የታገዙ በርካታ አካባቢዎችን መቆጣጠራቸዉና በጦርነቱ የበላይነትን መያዛቸዉ እየተነገረ ነዉ። ትልቋ የሶርያ ከተማ የሆነችዉና በአማፅያን ተይዛ የቆየችዉን የአሌፖ ከተማን ለመቆጣጠር በሚያስችል ሁኔታ የአሳድ ወታደሮች ከተማዋን እንደከበቡ እየተነገረ ባለበት ሁኔታ ነበር ባለፈዉ ሃሙስ ዩኤስ አሜሪካና ሩስያ የሶርያ ተፋላሚ ወገኖች ተኩስ አቁመዉ ወደ ሰላም ድርድር እንዲመጡ መስማማታቸዉ የተገለፀዉ። ይሁን እንጂ ቱርክ ባለፉት ሁለት ቀናት በሶርያ «IS»ን ከሚዋጉት ኃይሎች ጋር አብሮ በመዋጋት የሚታወቀዉን « YPG» የተሰኘዉን የኩርድ ሕዝባዊ ጦር በመድፍ በመደብደብ በሰሜን ምስራቅ ሶርያ የተቆጣጠሩዋትን አካባቢ እንዲለቁ ጠይቃለች። ዝርዝሩን የብራስልሱ ወኪላችን ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ