ቱርክ እና የአሜሪካን የኒዩክልየር ጦር መሣሪያዎች
ሰኞ፣ ነሐሴ 16 2008ማስታወቂያ
የቱርክ እና የአውሮፓ ህብረት እንዲሁም የቱርክ እና የዩናይትድ ስቴትስ ግንኙነት እየሻከረ ሄዷል ። በተለይ ከመንግሥት ግልበጣ ሙከራው በኋላ የአንካራ መንግሥት የዩናይትድ ስቴትስ እጅ አለበት ብሎ መክሰሱ ውዝግቡን አባብሶታል ። በቱርክ እና በቱርክ አጎራባች አገሮች የሚታየው እንቅስቃሴ እን የቦምብ ጥቃቶችም እንዲሁም ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው ቡድን ሽብር ፈጠራም የአሜሪካንን መንግሥት እያሳሰበው መጥቷል ። አሜሪካን ቱርክ የሚገኙት የጦር መሣሪያዎቿ ባልታወቁ ወገኖች እጅ እንዳይገባ ከቱርክ እናውጣ የሚለው ሃሳብ አሁን እየተጠናከረ መጥቷል ። በዚህ ላይ አትኩሮ የተካሄደ የአንድ ጥናት ውጤትን ያካተተ ዘገባ በቅርቡ ይፋ ተደርጓል ።የዶቼቬለው አንድርያስ ቤከር ያጠናቀረውን የዘገባውን ፍሬሃሳቦች ይልማ ኃይለ ሚካኤል እንደሚከተለው አሰባስቦታል ።
አንድርያስ ቤከር /ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ