ተሸላሚ ያጣው የሞ ኢብራሂም ሽልማት
ሰኞ፣ ጥቅምት 4 2006ማስታወቂያ
ሞኢ ኢብራሂም የተባለው ድርጅት በመልካም አስተዳደር ለተመረጡ የአፍሪቃ መሪዎች ለሚሰጠው ሽልማት በዚህ ዓመት መስፈርቱን ያሟላ መሪ አለማግኘቱን አስታወቀ ። ድርጅቱ ዛሬ ለንደን ውስጥ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በዚህ ዓመት ተሸላሚ እንደሌለ አስታውቋል ። ከ52 የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች መካከል የድርጅቱን መስፈርት ያሟላ መሪ አለመገኘቱ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አነጋጋሪ ጉዳይ ነበር ። ድርጅቱ ለአፍሪቃ ሃገራት የሰጠው የመልካም አስተዳደር ደረጃም ዛሬ ይፋ ሆኗል ። የለንደኑ ዘጋቢያችን ድልነሳ ጌታነህ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ድልነሳ ጌታነህ
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ