ተስፋ አስቆራጩ የኃይል መቆራረጥ
ዓርብ፣ መጋቢት 15 2009ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ ኬንያ፤ሱዳን እና ጅቡቲ የኤሌክትሪክ ኃይል ትሸጣለች። አዳዲስ የኃይል ማመንጫዎች በመገንባት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ እነ ታንዛኒያ እና የመንን ከደንበኞቿ መካከል ልታደርግም አቅዳለች። የኃይል አቅርቦቱም ሆነ የአገልግሎት አቀራረቡ ግን በኢትዮጵያውያን ዘንድ ወቀሳ ይበዛበታል። የሆለታ፤ሎጊያ ወልዲያ ከተሞች ነዋሪዎች እንደሚሉት የኃይል መቆራረጡ በለት ተለት ሕይወታቸው ላይ ጫና አሳድሯል።
በዋትስ አፕ አስተያየታቸውን ያደረሱ አድማጮቻችን እንደሚሉት ጅማ አካባቢ የመቆራረጥ ችግር የተለመደ ነው፤በአዳማ ከተማ ቀበሌ አስራ አራት መብራት በቀን በአማካኝ ሶስት ጊዜ ይጠፋል። በኃይል መቆራረጥ ሳቢያ ወሎ ውርጌሳ «ሕብረተሰቡ ከፍተኛ ችግር ላይ ነው። በተለይ ወፍጮና ዳቦ ቤት።» የኢትዮጵያ መንግሥት የኃይል አቅርቦቱም ይሁን የአገልግሎት አሰጣጡ ያሉበትን ችግሮች ለመፍታት በተደጋጋሚ ቃል ቢገባም በተግባር የታየው ግን ዜጎችን አላረካም።
እሸቴ በቀለ
አርያም ተክሌ