ቦምብ ለማፈንዳት በመሞከር የተያዘው ሶማሊያዊ አሜሪካዊ
ሰኞ፣ ኅዳር 20 2003ማስታወቂያ
ወጣቱ በጅሀድ ለመሳተፍ ባለፈው ዓመት ፓኪስታን መሄድ ስለ ሚችልበት ሁኔታ እዚያ ከሚገኝ አንድ ግለሰብ ጋር በኢሜል መልዕክት ይለዋወጥ እንደነበር ለፍርድ ቤት የቀረቡ መረጃዎች ያስረዳሉ ። የሚኒሶታው የማካሊስታር ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር አህመድ ሳማታር ለዶይቼቬለ እንደተናገሩት ሶማሊያዊ አሜሪካውያን ስማቸው ከሽብር ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ መነሳቱ በሶማሊያ አሜሪካዋን ላይ አሉታዊ ጫና ያሳድራል ። አበበ ፈለቀ ከዋሽግተን ዲሲ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
አበበ ፈለቀ ፣ ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ