ብርድ ልብስ ለጎደና ተዳዳሪዎች
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 16 2005ማስታወቂያ
የዘንድሮዉ የኢትዮጵያ ክረምት ክፉኛ ያቆረምዳል አሉ።በተለይ መሸትሸት ሲል የሚኖሩበት እንደሚሉት አያድርስ ነዉ።እቤታችን ሆነን እንዲሕ የበረደን ትላለች ወጣትዋ ጋዜጠኛ በረንዳ አዳሪዎችስ? መልስ አልጠበቀችም።ታዉቀዋለች።እና ለኒያ ግፉዓን የሚሰጥ ብርድልብስ ለማሰባሰብ ዘመቻ ጀመረች።በፌስ ቡክ የከፈተችዉን ዘመቻ «አንድ ብርድ ልብስ ለአንድ ጎዳና አዳሪ» በሚል ሥም ሰይማዋለች።ከያዘለት ለአዲስ አበባ የጎዳ አዳሪዎች አምስት ሺሕ ብርድ ልብስ ለመሰብሰብ ነዉ ዕቅዷ።ዕቅዷ ግብ መታም ሳተ-ጀምራዋለች።የሕዝቡን ምላሽ «አስደሳች» ትለዋለች።ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር አነጋግሯታል።
ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ