1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብርሃን በኢትዮጵያውያን የተቋቋመ ማህበር

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 10 2004

በአኽን ከተማ ነዋሪ በሆኑ ጥቂት ኢትዮጵያውያን ተመስርቶ አሁን ጀርመናውያንና ከጀርመን ውጭ የሚገኙ አባላት ያሉትን ብርሃን የተባለውን ማህበር ነው የሚያስቃኘን የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ።

https://p.dw.com/p/15ZAz
24.12.2011 hin und weg aachen 1

በአኽን ከተማ ነዋሪ በሆኑ ጥቂት ኢትዮጵያውያን ተመስርቶ አሁን ጀርመናውያንና ከጀርመን ውጭ የሚገኙ አባላት ያሉትን ብርሃን የተባለውን ማህበር ነው የሚያስቃኘን የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ። ምዕራብ ጀርመን በሚገኘው በአኽን ከተማ በኢትዮጵያውያን የተመሰረተው ብርሃን የተባለው ማህበር ሊቀ መንበር አቶ እሸቱ ውንድአፍራሽ ናቸው ስለማህበሩ አመሰራረትና ዓላማ ያስረዱን ። አቶ እሸቱ ወደ 37 ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ጀርመን ኖረዋል ። ከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል በመጡባት ጀርመን በሚካኒካል ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝተዋል ። ከዚያም የድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ሃገር ቤት በመሄድ ለ ጥቂት ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ፋከልቲ በመምህርነት ካገለገሉ በኃላ እንደገና ወደ ጀርመን ተመልሰው ትምህርታቸውን አጠናቀዋል ። አቶ እሸቱ ትዳር መስርተው ኑሮአቸውን እዚሁ ጀርመን ያደረጉ የቤተሰብ ሃላፊም ናቸው ። በአሁኑ ጊዜ ለኢትዮጵያውያን ለኤርትራውያንና እንዲሁም ሌሎችም የውጭ ዜጎችና ለጀርመናውያን ከጤና አጠባበቅ ጋር የተያያዙ ሴሚናሮችን በግል ይሰጣሉ ። ከግል ሥራቸው ጎን ለጎን ብርሃን ማህበርን በሊቀመንበርነት የሚመሩት አቶ እሸቱ እንደተናገሩት ማህበራቸው በተቋቋመበት ዓላማ መሰረት ኢትዮጵያ ለሚገኙ አንዳንድ ድርጅቶች እርዳታ ሲለግስ ቆይቷል ።

በዚህ መልኩ ሲንቀሳቀስ የቆየው ብርሃን በ1997 በጎሮጎሮሳውያኑ በ 2005 የአባላቱ ቁጥር መመናመን ጀመረ ።
ድምፅ
ብርሃን ማህበር በጀርመን መንግሥት ድጋፍ በኢትዮጵያ የልማት እንቅስቃሴዎች ውስጥ አስተዋፅኦ የማድረግ እቅድም አለው ።

 

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ