ብሪታንያ እና የአዉሮጳ ሕብረት አባልነቷ
ዓርብ፣ ግንቦት 9 2005ማስታወቂያ
የብሪታንያ ፖለቲከኞች ሐገራቸዉ የአዉሮጳ ሕብረት አባል እንደሆነች ትቀጠል-አትቀጥል በሚለዉ ሐሳብ ዳግም የገጠሙት ዉዝግብ የጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካሜሩንን መንግሥት እየገዘገዘዉ ነዉ።ጠቅላይ ሚንስትሩ ብሪታንያ በሕብረቱ አባልነት መቀጠል-አለመቀጠሏን የሐገሪቱ ሕዝብ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር በ2017 በድምፁ እንደሚወስን ከዚሕ ቀደም አስታዉቀዉ ነበር።በቅርቡ በተደረገዉ የከተሞች አስተዳደር ምርጫ የጠቅላይ ሚንስትሩ ወግ አጥባቂ ፓርቲ በርካታ መቀመጫዎችን ማጣቱ፥የሐገሪቱ ምጣኔ ሐብት ይበልጥ ማሽቆልቆሉና ከምሥራቅ አዉሮጳ ወደ ብሪታንያ የሚገባዉ ሕዝብ ቁጥር መጨመሩ የአዉሮጳ ሕብረት የብሪታንያን ሉዓላዊነት እየተጋፋ ነዉ የሚሉ ወገኖችን ቅሬታ አጠናክሮቷል።በዚሕም ምክንያት የጠቅላይ ሚንስትሩ ፓርቲ ሚንስትሮች እና የምክር ቤት አባላት ሳይቀሩ የካሜሩንን አቋም እየተቃወሙ ነዉ።የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ድልነሳ ጌታነሕ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ