ብሩክ የሺጥላ እና ስዕሎቹ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 24 2006ማስታወቂያ
ሰዓሊ ብሩክ የሺጥላ እስካሁን አንድ በጋራ እና ሶስት ደግሞ የግል አውደ ርዕዮችን ለተመልካች አቅርቧል። ብሩክ የስዕሎቹን ይዘት እና መልዕክት አጫውቶናል።
ከዚህም ሌላ ልደቱን ነገ ያከብራል። ዕለቱ ግን የተወለደበት ቀን አይደለም። ልደቱን አስቀድሞ ማክበር ያስፈለገበት ምክንያት የተወለደበት ቀን ትልቅ ቀዶ ህክምና ስለሚኖረው ነው። ይህ ብቻ አይደለም።
ካለፉት ሰባት አመታት አንስቶ ልደቱን ከጓደኞቹ ጋር ተሰባስቦ ሲያከብር፤ ወጣቱ የሚያከብርበትን ገንዘብ ለሌሎች የሚጠቅሙ ነገሮችን በመግዛት ወይም በማድረግ እንደሚያሳልፍ ገልፆልናል። ያለፈውን ዓመት ለምሳሌ ድሮ ለተማረበት ት/ቤት የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች መፅሀፍ ሲገዛ፤ ለዚህኛው አመት ደግሞ አዲስ እቅድ አለው። የብዙ ሰዎችን ህይወት ለማትረፍ ሰዎችን ሰብስቦ ደም እንዲለግሱ ያደርጋል።
ብሩክ ከቀዶ ህክምናው በኋላ አዲስ አውደ ርዕይ ለማሳየት አላማ እንዳለው ነግሮናል። ከዛ በፊት የብሩክን ስዕሎች ለማየት ለምትፈልጉ አድማጮች ድረ ገፁ www.brookyeshitila.comነው።
ከብሩክ የሺጥላ ጋር የነበረንን ቆይታ ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።
ልደት አበበ
ተክሌ የኋላ