ቤተ እስራኤላዉያንና የእስራኤል ውሳኔ
ረቡዕ፣ ሐምሌ 10 2005ማስታወቂያ
የእስራኤል መንግሥት ከኢትዮጵያ የመጨረሻ ተጓዞች ናቸው ያላቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ በጎንደር ከተማ ይጠባበቁ የነበሩ ቤተ እስራኤላውያን ነሐሴ 28 2013 ተጠቃለው እስራኤል እንደሚገቡ አስታውቋል ። ይህ ውሳኔም በአዲስ አበባና በጎንደር ከተማ ተፈናቅለው ወደ እሥራኤል ለመግባት በተስፋ ይጠባበቁ የነበሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ የቤተ እስራኤላውያን ቤተሰቦችን አስጨንቋል ። እስራኤል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ይሁዲዎችም ውሳኔውን በመቃወም ሠላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል ። ግርማው አሻግሬ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል ።
ግርማው አሻግሬ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ