ባራክ ኦባማና የምጣኔ ሀብት መደጎሚያ ዕቅዳቸው
ማክሰኞ፣ የካቲት 3 2001ማስታወቂያ
ኦባማ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስገነዘቡት ዋነኛ ግቡ አሜሪካውያንን መልሶ የስራ ባለቤት ማድረግ የሆነው የምጣኔ ሀብት መደጎሚያ ዕቅድ ተግባራዊ ሲሆን አራት ሚሊዮን ስራ ይፈጥራል ። ፕሬዝዳንቱ የሀገሪቱ የምጣኔ ሀብትን መዋቅር ወደ ነበረበት ፣ለመመለስ ገበያውን ለማረጋጋት እና ህብረተሰቡም በመዋቅሩ ላይ ዕምነት እንዲኖረው ግልፅነት እና ተጠያቂነትን ያካተቱ የአሰራር ስልቶች እንደሚዘረጉም ጠቁመዋል ። ከዋሽንግተን ዲሲ አበበ ፈለቀ ዝርዝር ዘገባ አለው