1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባልካን፥ የጎርፍ መጥለቅለቅ ሕይወት አጠፋ

እሑድ፣ ግንቦት 10 2006

በባልካን ሃገራት እና መካከለኛው አውሮጳ ውስጥ በደረሰዉ ከፍተኛ የዉሃ መጥለቅለቅ የሟቾች ቁጥር ከ 30 በላይ መድረሱ ተነገረ። በደቡብ ምሥራቅ አዉሮጳ ከሚገኙ ነዋሪዎች መካከል ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በዉኃ መጥለቅለቁ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

https://p.dw.com/p/1C27j
ምስል Reuters

በቦስንያ-ሄርዞጊቪና 60 ሺህ ነዋሪዎች፣ በሰርቢያ 95 ሺህ ነዋሪዎች በዉኃ መጥለቅለቁ ምክንያት የኤሌትሪክ አገልግሎት ተቋርጦባቸዋል። በደቡብ ምሥራቅ አዉሮጳ የአየር ንብረት ጉዳይ መረጃ መሰብሰብ ከጀመረበት ከዛሬ 120 ዓመት ወዲህ ከባድ የዉኃ መጥለቅለቅ ያስከተለ ዝናብ ሲዘንብ ይህ ለመጀመርያ ጊዜ እንደሆነ ተነግሯል።

በባልካንና መካከለኛው አውሮጳ ለሠዓታት ባለማቋረጥ የጣለው ወጀባማ ዝናብ የፈጠረው የጎርፍ መጥለቅለቅ የተከሰተው ዝናቡ ከ30 ሠዓታት በላይ ያለማቋረጥ በመውረዱ የተነሳ እንደሆነ ተነግሯል። ትናንት ቦስኒያ ውስጥ አንድ ሰው፣ አራት ሰዎች ደግሞ ሠርቢያ ውስጥ መሞታቸው ተዘግቧል።

በዝናቡ የተነሳ ስሎቫኪያ ውስጥ አንድ ሰው መሞቱ ሲነገር፤ ሠርቢያ የአስቸኳይ ጊዜ አውጃ ሩስያንና የአውሮጳ ኅብረትን ርዳታ ተማፅናለች። ርዳታ የተጠየቁ ሃገራት
የነፍስ አድን ሠራተኞችንና ቁሳቁሶችን መላካቸውን አስታውቀዋል። ጀርመን የበጎ ፈቃድ ሰራተኞችን ወደ ቦታው ልካለች። በዝናቡ የተነሳ 135,000 ሰዎች የኤሌክትሪክ አቅርቦት የተቋረጠባቸው ሲሆን፤ በርካታ ከተሞችና መንደሮች ሰብረው በወጡ ወንዞች ተጥለቅልቀዋል። ዝናቡ መጣል የጀመረው ከትናንት በስትያ ጠዋት ነበር።

የጎርፍ መጥለቅለቁ ቦስንያ ውስጥ 30 ሰዎችን ሲገድል፤ ሠርቢያ ውስጥ ተጨማሪ ሦስት ሰዎች መሞታቸው ታውቋል። እስካሁን ድረስ 20,000 ሠርቦች ከመኖሪያቸው እንዲለቁ ተደርጓል። ጎርፉ እየጨመረ እንደሚሄድ በመነገሩ የወንዝ ተፋሰስ ዳርቻዎች ዛሬ አሸዋ በሞሉ ከረጢቶች ክምር ሲገደቡ ውለዋል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ

የጎርፍ መጥለቅለቅ ሠርቢያ
የጎርፍ መጥለቅለቅ ሠርቢያምስል Reuters/Marko Djurica