1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባህላዊዉ መጠጥ ጠላ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 19 2003

ጠላ በማቶት እንጀራ በሌማት፣ ጠላ ያለ አተላ ጠጅ ያለ አንቡላ፣ ጠላና ጎተና በአንድ ቀን አይደርስም፣ ጠላ ካሰከረዉ ወተት ያሰከረዉ፣ ጠላ ከስር ነገር ከአገር፣ ጠላዉ ሳይገባ ማቶቱ፣ ቀንዱ ሳይገባ ጅራቱ፣

https://p.dw.com/p/Ri0b
ምስል Peter Zimmermann

ጠላ ባእድ አሳላፊ ዘመድ፣ ጠላ ሲሉት ሽምጥጥ ኮሶ ሲሉት ስቅጥጥ፣ ጠላ ባለቤቱን አያዉቅም፣ የሚባል ጠላን ያስታከከ ምሳሌያዊ አነጋገር አለ።

እንቢ ጠላ ጠላ ቅራሪ ቅራሪ፣

እሞትለታለሁ ለዝያ ለተማሪ፤

የማናት ወይዘሮ የማናት ቀምጣላ፣

በአንገትዋ ይወርዳል የምትጠጣዉ ጠላ፤ እየተባለ ባህላዊዉ እና ጥንታዊዉ የኢትዮጽያዉያን መጠጥ ይነገርለታል። የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችን አቅፋ በምትገኘዉ ኢትዮጽያችን ዉስጥ በርካታ ባህላዊ ምግቦች እና መጥጦች መካከል ጠላ የብዙ አመታትን ታሪክ ካስቆጠሩ መጥጦች መካከል አንዱ እንደሆነ ይነገርለታል። አሁን አሁን በተለይ በከተማዉ አካባቢ ቢራና ሌሎች መጠጦች መጡና የጠላ ጉዳይ ቀረት ያለ ይምሰል እንጂ በተለይ በገጠሩ ቤት ጠላ እና ቆሎ ካልተገኘ በአካባቢዉ ላይ ችግር እንዳለ መቆጠሩ ይደመጣል። ታድያ አዲስ አመት፣ ሰርግ፣ ማህበር ሲመጣ ያለ ጠላ እና ዳቦ በአሉ በአል እንደማይመስል የታወቀ ነዉ።

ዝግጅቱን ከዚህ ያድምጡ፤


አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ