በፀሀይ የምትሰራ አይሮፕላን የሙከራ በረራ
ረቡዕ፣ ግንቦት 10 2003ማስታወቂያ
የሁለት ሲውዘርላንዳዊያን የስራ ውጤት የሆነችው አይሮፕላን፤ ከ ሲውዘርላንድ ተነስታ ከ 12 ሰዕት 59 ደቂቃዎች በኋላ ብራስልስ ላይ ስታርፍ በጠቅላላ የተጓዘችው 600 ኪሎ ሜትር ገደማ ነበር። አይሮፕላኗ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ከሲውዘርላን የአየር ሀይል ተነስታ፤ በፈረንሳይና ሉክሱንበርግ ላይ በራ፤ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ግድም ነበር በፖሊስ ሄሊኮፕተር ታጅባ ቤልጄም መዲና ብራስልስ ያረፈችው። ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ በአዲስ አበባ ዮንቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲቱት፤ የኤሌክትሪካልና ኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ ክፍል ኃላፊ በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያም አድርገዋል።
ልደት አበበ
ሂሩት መለሠ