1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጋዛ እና እስራኤል ድንበር ዝምታ ነግሷል

ሰኞ፣ ሚያዝያ 28 2011

ሰላማዊ ሰዎችን ጨምሮ 21 ፍልስጤማውያን እና አራት እስራኤላውያን የተገደሉበት የጋዛ ሰርጥ ውጊያ ግብፅ ለግልግል ጣልቃ ከገባች በኋላ በርዷል። ከሶስት ቀናት በፊት የተቀሰቀሰው ውጊያ በተለይ በዕለተ እሁድ አይሎ የነበረ ሲሆን ከሁለቱም ወገን በአጠቃላይ 25 ሰዎች ተገድለዋል።

https://p.dw.com/p/3I1EZ
Gaza-City Zerstörungen nach Luftangriffen aus Israel
ምስል Reuters/S. Salem

የጋዛ ውጊያ

ሰላማዊ ሰዎችን ጨምሮ 21 ፍልስጤማውያን እና አራት እስራኤላውያን የተገደሉበት የጋዛ ሰርጥ ውጊያ ግብፅ ለግልግል ጣልቃ ከገባች በኋላ በርዷል። ከሶስት ቀናት በፊት የተቀሰቀሰው ውጊያ በተለይ በዕለተ እሁድ አይሎ የነበረ ሲሆን ከሁለቱም ወገን በአጠቃላይ 25 ሰዎች ተገድለዋል። ከአምስት አመታት ወዲህ ኃይለኛ የተባለው የሁለቱ ወገኖች ውጊያ ግብፅ ጣልቃ ከገባች በኋላ በተኩስ አቁም ስምምነት መብረዱን ሁለት የፍልስጤም ባለሥልጣናት እና ንብረትነቱ የሐማስ የሆነ አንድ የቴሌቭዥን ጣቢያ አረጋግጠዋል። ከእስራኤል በኩል ግን እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ይልማ ኃይለሚካኤል ተጨማሪ ዘገባ አለው። 

ይልማ ኃይለሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ