በጉራፈርዳ የተካሄደዉ ባህላዊ እርቀ ሰላም እና ዉዝግቡ
ሰኞ፣ ጥቅምት 15 2014ማስታወቂያ
በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በአካባቢያቸው ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ያስችላል የተባለ የባህላዊ እርቀ ሠላም ሥነ-ስርዓት ተካሄደ።
የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የባህላዊ እርቀ ሠላም ሥነ-ስርዓት በአካባቢውን ሰፍኖ የቆየውን ሞትና መፈናቃል ለማስቀረት ያስችላል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል። ዶቼ ቬለ (DW) ያነጋገራቸው የወረዳው ተፈናቃዮች በበኩላቸው እርቀ ሠላም መካሄዱ መልካም መሆኑን በመጥቀስ ተመሳሳይ ክስተቶች እንዳይደርሱ እርቀ ሰላሙ የሕግ ድጋፍ ያስፈልገዋል፤ መንግስትም ህግ መስከበሩ ላይ ሊበረታ ይገባል ብለዋል።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ