የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በ12 ከተሞች 86,000 ተፈናቃዮችን ለማስፈር ጥረት ላይ ነው
ረቡዕ፣ ጥር 30 2010ማስታወቂያ
ከኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ የድንበር አካባቢዎች የተፈናቀሉ 584,000 ዜጎች ወደ ቀደመ መንደራቸው መመለስ ቅድሚያ ተሰጥቶታል። ቀሪዎቹ ተፈናቃዮች በሌሎች አካባቢዎች የሚሰፍሩ ይሆናል። የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በበኩሉ በ12 ከተሞች 86,000 ተፈናቃዮችን ለማስፈር ጥረት በማድረግ ላይ ነው። በተመረጡ 12 ከተሞች 12,000 የመኖሪያ ቤቶች በመገንባት ላይ ናቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት በድንበር ውዝግቡ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የሚገኙባቸውን ቆሎጂ 1 እና ቆሎጂ 2 የተባሉ መጠለያዎች ለመዝጋት መወሰኑንም አስታውቋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች የድንበር ውዝግብ ከአንድ ሚሊዮን በላይ መፈናቀላቸውን ቀደም ብሎ መግለፁ አይዘነጋም።
መክብብ ሸዋ
እሸቴ በቀለ