በድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የተጠረጠሩት ተበየነባቸዉ
ሐሙስ፣ የካቲት 18 2013ማስታወቂያ
ኢትዮጵያዊዉን ድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳን በመግደል፣ማስገደልና በአባሪ ተባባሪነት ከተጠረጠሩት 4 ተከሳሾች 3ቱ እንዲከላከሉ ተበየነባቸዉ።ዛሬ አዲስ አበባ ያስቻለዉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባሳለፈዉ ብይን መሠረት አንደኛዉ ተከሳሽ ጥላዬ ያሚ በተከሰሰበት የወንጀል ጭብጥ ጥፋተኛ መሆኑ ተበይኖበታል።በአባሪ ተባባሪነት የተጠረጠሩት ሁለተኛና ሶስተኛ ተከሳሾች ከዚሕ ቀደም የተጠቀሰባቸዉ የክስ አንቀፅ ተሻሽሎ በተለያዩ የሕግ አንቀፆች እንዲጠየቁ ችሎቱ በይኗል።አራተኛዋን ተከሳሽ ላምሮት ከማግል ግን በነፃ እንድትሰናበት ችሎቱ አዝዟል።
ስዩም ጌቱ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ