1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

14 ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ

ሐሙስ፣ መስከረም 28 2013

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጋሹ ዱጋስ በበኩላቸው ማክሰኞ ዕለት በዳንጉር ወረዳ በተሸከርካሪ ላይ ጥቃት መድረሱንና የ14 ሰዎች ህይወት ማለፉን አረጋግጠዋል። በዕለቱ ኮማንድ ፖስት ኦፕሬሽን እያከናወነ እንደነበረና ማንም ተሸከርካሪ እንዳያልፍ መልእክት ተላልፎ ነበር ብለዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3jd44
Karte Äthiopien Metekel EN

በዳንጉር 14 ሰዎች በታጣቂዎች፣14 ታጣቂዎች ደግሞ በጸጥታ ኃይሎች ተገደሉ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዳንጉር ወረዳ ከትናት በስትያ  በታጠቂዎች በተፈፀመ ጥቃት የአስራ አራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።እንደነዋሪዎቹ ታጣቂዎቹ  በዳንጉር ወረዳ ጉብ ላክ በተባለ  ቀበሌ ተሳፋሪዎችን ከመኪና አውረዳዋቸው ነው የገደሉዋቸው።የመንግሥት መገናኛ ዘዴዎች በበኩላቸው የአካባቢው ጸጥታ አስከባሪዎች 14 ታጣቂዎች መግደሉን አስታውቀዋል። በወረዳው ቤንገዝ በተባለ ቀበሌም መስከረም 14 በታጣቂዎች በደረሰው ጥቃት  የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል። የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጋሹ ዱጋስ በበኩላቸው ማክሰኞ ዕለት በዳንጉር ወረዳ በተሸከርካሪ ላይ ጥቃት መድረሱንና 14 ሰዎች ህይወት ማለፉን አረጋግጠዋል። በዕለቱ ኮማንድ ፖስት ኦፕሬሽን እያከናወነ እንደነበረና ማንም ተሸከርካሪ እንዳያልፍ መልእክት ተላልፎ ነበር ብለዋል፡፡ አካባቢው ወደ ሰላማዊ ሁኔታ እኪመለስ ድረስ ከመተከል ወደ ጉባ መስመር ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተደርጓልም ብለዋል።ነጋሳ ደሳለኝ ከአሶሳ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።

ከትናንት በስቲያ ከአሶሳ  ወደ ግልገል በለስ ከተማ ሲያቀና የነበረው ተሽከርካሪ በዳንጉር ወረዳ ጉብ ላክ በተባለ ቀበሌ ሲደርስ በአካባበው ይንቀሳቀሳሉ የተባሉ ታጣቂዎች ተሳፋሪዎችን በማውረድ አራት ሰው ተኩሰው መግደላቸውን የአንድ አካባቢው ነዋሪ በስልክ ተናግረዋል። በሌላ ጭነት መኪና ተሳፍረው ወደ ግልገል በለስ ከተማ ይሄዱ በነበሩ ሌሎች ተሳፋሪዎች ላይም ባደረሱት ጥቃት የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ነዋሪዎቹ አስረድተዋል። በጉብ ላክ ቀበሌ ከመኪና ሰው በማውረድ ሲያንገላቱ ከነበሩ ታጠቂዎች መካከልም በጸጥታ ሀይሎች እርምጃ የተወሰደባውና በቁጥጥር ስር የዋሉ መኖራውን የተናገሩ ሲሆን  ታጠቂዎቹም በአካቢው የሚታውቁ ሰዎች ናቸው ብለዋል። 
መሰከረም 14 በቤንዝ ቀበሌ በአርሶ አደሮች ላይ በደረሰው ጥቃት ምክንያትም ብዙ ቁጥር ያላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ሌላ ስፍራ መሸሻቸውን የገለጹት ሌላው የማንቡክ ነዋሪም በጉብላክ ቀበሌ በደረሰው ጥቃት ምክንያትም ጉዳት የደረሰባቸው 15 ሰዎችም ለህኪምና መላካቸውን አመልክተዋል።
በተደጋጋሚ በታጠቂዎች ጥቃት የሚደርስበት መተከል ዞን አምስት የሚደርሱ ወረዳዎችም በኮማንድ ፖስት እየተጠበቁ ይገኛሉ፡፡  በመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች  ታጥቀው በሚንቃሳቀሱ አካላት ተደጋጋሚ  ጥቃቶች  ለበርካታ ሰው  ህይወት ማለፍንና ንብረት ውድመት ምክንያት መሆናቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጋሹ ዱጋስ አካባቢው ሰላም መሆኑ እስኪረጋገጥ ድረስ  ተሸከርካሪ ከአሶሳ ወደ ግልገል በለስ ከተማ እንዳይንቀሳቀስ መደረጉን አስታውቀዋል።ከትናት በስቲያም የጸጥታ ችግር መኖሩን ተነግሮ እንደነበር በመግለጽ በኮማንድ ፖስት የተላለፈው መልዕክት ባለመቀበል ህዝብን ሲያመለሱ በነበሩ  ሰዎች  ምክንያት የደረሰ ጥቃት እንደሆነ ገልጸዋል።ከሞቱት መካከከልም አንድ ቻይናዊ ይገኝበታል ብለዋል።በመተከል ዞን እየተስተዋለ ያለውን የጸጥታ ችግር ለመቅረፍ የአካባቢው ኮማንድ ፖስት በየዕለቱ  ኦፕሬሽ በማከናውን ወደ በዜጎች ላይ ችግር የሚፈጠሩ አከላት ላይ እርምጃ እየወሰዱ እነደሚገኝም ኀላፊው አክለዋል፡፡  በዞኑ ጸጥታን ለማስከበርም ሆነ ባጠቃላይ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም ያላቸውን ከ40 በላይ የክልል፣ የዞን እና የወረዳ አመራሮችን ከስራ ማገዱን የክልሉ መንግስት ከሳምንት በፊት መግለጹም የሚታወስ ነው።

Äthiopien Binishangul Gumuz  Region Metekel Zone Gilgel
ምስል DW/Negassa Desalegn

ነጋሳ ደሳለኝ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ