1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በደቡብ ክልል የሚገኙ እሥረኞች የሰብዓዊ መብት ይዙታ

ሰኞ፣ ጥቅምት 7 1998

ዓለም ሕጎችን በሚያከብሩ ሀገሮች ውስጥ መሠረታዊው የሰብዓዊ መብት የሚከበርበት ጥያቄ ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው።

https://p.dw.com/p/E0jP

ሰዎች ሲታሠሩ በተወሰነ ደረጃ ነፃነታቸው ይገፈፋል፤ ሰብዓዊ መብታቸውም ጥያቄ ውስጥ ይገባል፤ ይህ ግን በአግባቡ በጊዜው የመዳኘት መብታቸውን ጭምር ያጣሉ ማለት አይደለም። የእሥረኞች አገልግሎት ኅብረት በኢትዮጵያ ደቡብ ክልል ማረሚያ ቤቶች ያሉ እሥረኞች በአግባቡ ተዳኝተው እንደሆነና ጉዳያቸው የተጓተተባቸውን እሥረኞች ሁኔታ ለመመርመር እንዲቻል ከደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር ተባብሮ የማጣራት ሥራ አካሂዶዋል፤ እብረቱ በዚሁ ሥራው፡ ወኪላችን ፀጋዬ እንደሻው የዳኝነት ማሻሻያ ፕሮዤ ተጠሪ አቶ ሲሳይ ገመቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፡ በርካታ መዘርዝሮችን መርምሮ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች ለውሳኔ አብቅቶዋል።