በዛክሰን አንሀልት የተስፋፋው የውጭ ዜጎች ጥላቻ29 መጋቢት 2007ማክሰኞ፣ መጋቢት 29 2007በጀርመን የዛክስን አንሀልት ፌዴራዊ ክፍለ ሀገር በምትገኘው የትረግሊትስ ከተማ ባለፈው የሳምንት መጨረሻ በአንድ ለስደተኞች በተዘጋጀ መኖሪያ ህንፃ ላይ የተጣለውን አሳዛኝ የቃጠሎ ጥቃት ጀርመናውያን እና ፖለቲከኞቻቸው አውግዘውታል።https://p.dw.com/p/1F3hlየትረግሊትስ ነዋሪዎች በፀረ የውጭ ዜጎች ጥላቻ ሰልፍ ላይምስል picture-alliance/dpa/F.Benschማስታወቂያ የከተማይቱ ነዋሪዎችም ወንጀሉን በማውገዝ አደባባይ ከመውጣታቸውም ሌላ ስደተኞችን ተቀብለው ለማስተናገድ ዝግጁነታቸውንም አሳይተዋል። ወንጀሉን የፈፀሙት የቀኝ አክራሪዎች ሳይሆኑ እንደልቀሩ ጥርጣሬ ተሰምቶዋል። አሁን በወደመው የመኖሪያ ህንፃ ውስጥ በሚቀጥለው ወር 40 ስደተኞች ይገባሉ ተብሎ ነበር የተቀደው። ይልማ ኃይለ ሚካኤል አርያም ተክሌ ነጋሽ መሀመድ