በዐረብ ሀገሮች ያሉ ኢትዮጵያውያን ችግር
ቅዳሜ፣ መጋቢት 8 1999ማስታወቂያ
በመካከለኛው ምሥራቅ በሚገኙት ዐረባውያት ሀገሮች ውስጥ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሥራ ላይ ተሠማርተው ኑሮአቸውን በመምራት ላይ ይገኛሉ። ከነዚሁ መካከል ብዙዎቹ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥረው የሚሠሩ ሴቶች ሲሆኑ ከአሠሪዎቻቸው ብርቱ በደልና ሥቃይ እንደሚደርስባቸው፡ እንዲሁም፡ አንዳንዶቹ በትንንሽ ወንጀል በየወህኒ ቤቶች ውስት ኢሰብዓዊ በሆነ ሁኔታ በመማቀቅ ላይ እንደሚገኙ ራሳቸው ሰለባዎቹ እና ለሰብዓዊ መብት የሚሟገቱ ድርጅቶች በየጊዜው ከሚያወጡዋቸው ዘገባዎች ለመረዳት ተችሎዋል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ከተጎጂዎቹ፡ ችግራቸውን ለማቃለል ከሚሞክረው አዲስ አበባ ከሚገኘው ዓለም አቀፍ የማይግሬሽን መሥሪያ ቤት የሕገ ወጥ ፍልሰት ቢሮ ባለሥልጣን ወይዘሮ አሰፋች ኃይለሥላሤ፡ ከኢትዮጵያ የሠራተኞችና ማኅበራዊ መሥሪያ ቤት የሰው ኃይል ጥናትና ስታትስቲክስ ቡድን የሥራ ፈቃድ ሰጪ ክፍል ተወካይ ከአቶ ሳውድ መሀመድ፡ ከዐረብ ሀገሮች የተመለሱ ሰለባዎች ከመሠረቱት የጎመና ኢትዮጵያ ማኅበር ኃላፊ ከአቶ ዮናስ ታደሰ፡ እንዲሁም፡ በሳውዲ ዐረቢያ ጂዳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንሲላ ጀነራል አምባሳደር አቶ ተክለአብ ከበደ ጋር የተካሄደው ውይይት እንደሚከተለው ይደመጣል።