በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሠልፎች
ሰኞ፣ የካቲት 23 2001ማስታወቂያ
በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰኞ በብሪታንያ፣ በስዊድን፣ በኖርዌይና በስዊዘርላንድ መዲናዎች የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን፤ ማምሻውን በዩኤስ ዋሽንግተን ዲሲ እንደሚያደርጉም አስተባባሪዎቹ ገለፁ። የፍትህና አንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱ ካንሚደቅሳ፣ አርቲስት ቴዲ አፍሮና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞችም እንዲፈቱ፣ በሀገሪሪቱ የሠብዓዊ መብት እንዲከበር ሠልፈኞቹ ጥሪ አድርገዋል። የተቃውሞ ሠልፎቹ የሚደረጉት በአሜ ሪካን ኤምባሲዎች ደጃፍ መሆኑም ታውቓል።