በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የመድረክ መግለጫ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 13 2008ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ለሃገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል ።መድረክ በዚሁ መግለጫው በአወዛጋቢው የአዲስ አበባና የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ እቅድ መንስኤ በኦሮምያ በተነሱ ተቃውሞዎች በዜጎች ላይ ለደረሰ ሞት እንዲሁም ለወደመው ንብረት ተጠያቂ የሆኑ ለፍርድ እንዲቀርቡ ለመንግሥት ጥሪ አስተላልፏል ።መድረክ ከሌሎች ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የፊታችን እሁድ አዲስ አበባ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ቢጠይቅም ሰልፉን ማካሄድ እንደማይቻል መንግሥት መልስ እንደሰጠውም አስታውቋል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሀመድ