በእቃ መጫኛ አዉሮፕላን ተደብቆ ስዊድን የገባዉ ኢትዮጵያዊ
ማክሰኞ፣ የካቲት 29 2008ማስታወቂያ
ስለሰዉየዉ ማንነት እንዴት በዚህ መንገድ እዚህ ሊደርስ እንደቻለ ሚዲያዎች ያወጡት ሌላ ዝርዝር ዘገባ ባይኖርም ግለሰቡ መልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ተዘግቦአል። ነሐሴ ወር ውስጥ አንድ የ 24 ዓመት የኢትዮጵያ የአየር መንገድ ሰራተኛ እንደዚሁ በእቃ መጫኛ አውሮፕላን ውስጥ ሆኖ ስዊድን መግባቱ የሚታወቅ ሲሆን፤ ይህ ትናንት ይፋ የሆነዉ ክስተት በ7 ወራት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው። ምናልባት ከአዲስ አበባ ይህ አዲሱ መንገድ ሰዎችን በሕገ-ወጥ ማዘዋወርያ መንገድ ሳይሆን ሆኖ አይቀርም የሚል ጥያቄንም በብዞዎች ዘንድ አጭሮአል። በእቃ መጫኛ አዉሮፕላን ዉስጥ ተደብቆ ስዊድን ስለደረሰዉ ግለሰብ ሚዲያዎች ምን እየዘገቡ ነዉ። እዚህ ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት ስዊድን ስቶኮሆልም የሚገኘዉን ዘጋብያችንን ቲዮድሮስ ምሕረቱ አይቄዉ ነበር መልስ በመስጠት ይጀምራል።
ቴዮድሮስ ምሕረቱ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ