1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት

ረቡዕ፣ የካቲት 7 2010

እስረኞችን መፍታት ብቻ ውስብስቡን የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ችግር ሊፈታ እንደማይችል አሳስበዋል። ዶቼቬለ አስተያየታቸውን የጠየቃቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች መንግሥት የሀገሪቱን ችግር በዘላቂነት የሚፈቱ ተጨማሪ እርምጃዎችን እንዲወስድ ጥሪ አቅርበዋል።

https://p.dw.com/p/2si7S
Äthiopien Kaliti Gefängnis
ምስል DW/Y. Gebregziabher

የመድረክ አስተያየት

 

የኢትዮጵያ መንግሥት እስረኞችን መፍታት መቀጠሉን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አወደሱ። ሆኖም እስረኞችን መፍታት ብቻ ውስብስቡን የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ችግር ሊፈታ እንደማይችል አሳስበዋል። ዶቼቬለ አስተያየታቸውን የጠየቃቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች መንግሥት የሀገሪቱን ችግር በዘላቂነት የሚፈቱ ተጨማሪ እርምጃዎችን እንዲወስድ ጥሪ አቅርበዋል። ፓርቲዎቹ ከሰነዘሯቸው የመፍትሄ ሃሳቦች መካከል ሁሉን አሳታፊ ውይይት እንዲሁም ነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ ማካሄድ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት የሚሉት ይገኙበታል። የአራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ምክትል ሰብሳቢ ፕሮፌሰር በየነ ጵጥሮስ እርምጃው እንደዘገየ ፍትህ ይቆጠራል ብለዋል።የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ በበኩሉ መንግሥት የሚፈታቸውን መልሶ ላለማሰሩ ዋስትና የሚሰጡ እርምጃዎች እንዲወስድ ጠይቋል። የፓርቲው ዋና ፀሀፊ አቶ አዳነ ጥላሁን የፀረ ሽብሩ ህግ መሻሻል ወይም መቀየር አለበት ብለዋል። ተቃዋሚው አረና ትግራይ ደግሞ ዛሬ የተፈቱት ቀድሞውንም ሊታሰሩ አይገባም ነበር ብሏል። መንግሥት ከአሁን በኋላ ሊወስዳቸው ይገባል ያሏቸውን እርምጃዎችም ሊቀመንበሩ አቶ አብርሃ ደስታ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ