1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኤርትራ ላይ የቀረበው የሰብዓዊ መብት ረገጣ ወቀሳና ማስተባበያው

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 8 2001

መንበሩን ኒው ዮርክ ያደረገው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት፡ « ሂውመን ራይትስ ዎች » ዛሬ ይፋ ባወጣው ዘገባ መሰረት፡ የኤርትራ መንግስት እየፈጸመ ያለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ እጅግ አስከፊ ደረጃ ላይ ደርሶዋል።

https://p.dw.com/p/HYP9

ዘገባው እንዳመለከተው፡ የኤርትራ መንግስት ዜጎቹን ለከፍተኛ ስቃይ፡ ሰቆቃ፣ ለእስርና ለተራዘመ የብሄራዊ ውትድርና ዳርጎዋል። ስለዚሁ ወቀሳ አበበ ፈለቀ የድርጅቱን የአፍሪቃ ጉዳይ ተመልካችን ሌስሊ ሌፍኮውን አነጋግሮዋቸዋል። የአሥመራ ወኪላችን ጎይትኦም ቢሆን ያነጋገራቸው የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ፍስሀጽዮን ጴጥሮስ ለዶይቸ ቬለ በሰጡት ቃለምልልስ የ« ሂውመን ራይትስ ዎች » ወቀሳ በኤርትራ በኩል ውድቅ መሆኑን አስታውቀዋል።

አበበ ፈለቀ /ጎይትኦም ቢሆን /አርያም ተክሌ/ሸዋዬ ለገሠ