በኢትዮጽያ በተ.መ የአለም የምግብ ፕሮግራም ሰራተኞች ላይ የደረሰ ጥቃት
ማክሰኞ፣ ግንቦት 9 2003ማስታወቂያ
አደጋው ባልታወቁ ታጣቂዎች መጣሉን የሚገልጸዉ የአለም የምግብ ድርጅት በጥቃቱ አንድ ሰዉ መሞቱን እንዲሁም አንድ መቁሰሉን ሌሎች ሁለት ደግሞ የደረሱበት እንደማይታወቅ ገልጿል ። ሰራተኞቹ ጥቃቱ የተጣለባቸው ከጅጅጋ ተነስተው ጉለልቼ ወደተባለች ቀበሌ ሲጓዙ ነበር ። በአለም የምግብ ድርጅት ሰራተኞች ላይ በሶማሌ ክልል በፊቅ ዞን ስለደረሰዉ አደጋ የድሪደዋዉ ወኪላችን ዪሃንስ ገብረግዚአብሄር ዘገባ ልኮልናል
ዮሃንስ ገብረግዚአብሄር
አዜብ ታደሰ