በኢትዮጵያ የምግብ ተረጂው ቁጥር በቅርቡ ሊያሻቅብ እንደሚችል መጠቀሱ
ረቡዕ፣ ሐምሌ 22 2001ማስታወቂያ
ከስድስት ሚሊዮን በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በቅርቡ የምግብ ዕርዳታ ሊያስፈልጋቸው እንደሚችል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሠብዓዊ ጉዳዮች ጽቤት በእንግሊዘኛው ምህፃሩ ኦቻ ገለፀ። በኢትዮጵያ አደጋና መከ ላከል ዝግጁነት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሀላፊ አቶ ምትኩ ካሴ በበኩላቸው በኦቻ የተደረገው ጥናት በጋራ መሰራቱንና መግባባት ላይ መድረሱንም ገልፀዋል። ዝርዝሩን ታደሰ እንግዳው ከአዲስ አበባ ልኮልናል።
ታደሰ እንግዳው /ማንተጋፍቶት ስለሺ /አርያም ተክሌ